የሀገር ውስጥ ዜና

በአፈ ጉባኤ ታገሠ ጫፎ የሚመራ የፌደራል መንግሥት ከፍተኛ የልኡካን ቡድን ወደ መቀሌ አቀና

By Melaku Gedif

December 26, 2022

በአፈ ጉባኤ ታገሠ ጫፎ የሚመራ የፌደራል መንግሥት ከፍተኛ የልኡካን ቡድን ወደ መቀሌ አቀና

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፈ ጉባኤ ታገሠ ጫፎ የሚመራ የፌደራል መንግሥት ከፍተኛ የልኡካን ቡድን ወደ መቀሌ አቅንቷል፡፡

የልኡካን ቡድኑ ወደ መቀሌ ያቀናው የሰላም ስምምነቱን የትግበራ ሂደት ለመቃኘትና በስምምነቱ የተካተቱ ዋና ዋና ጉዳዮች በታቀደው መሠረት እንዲፈጸሙ ለማድረግ  ነው ተብሏል፡፡

የልኡካን ቡድኑ ከሁለት ዓመት በኋላ ወደ መቀሌ የተጓዘ የመጀመሪያው የፌዴራል መንግሥት ከፍተኛ ልኡክ ሲሆን÷ ስምምነቱ በመልካም ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ማሳያ መሆኑ ታምኖበታል።

በልዑካን ቡድኑ የብሔራዊ ምክክር ኮሚሽን አባላት መካተታቸውም የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የላከው መረጃ ያመላክታል፡፡