Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ካርቱም ገቡ

አዲስ አበባ፣ ጥር 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለሥራ ጉብኝት ሱዳን ካርቱም ገቡ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እና የልዑካን ቡድናቸው ወደ ካርቱም ያቀኑት ለአንድ ቀን የሥራ ጉብኝት መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እና ልዑካቸው ካርቱም ሲደርሱ የሱዳን ሪፐብሊክ የሽግግር ሉዓላዊ

ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ጄኔራል አብዱል ፈታሕ አል ቡርሃን አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

Exit mobile version