አዲስ አበባ፣ ሕዳር 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ቆዳ የሙቀት መጠንን መቆጣጠር ብቻ ሳይሆን ጤናማ፣ ጠንካራ እና ንቁ ሆነው እንዲቀጥሉ ከበሽታ፣ ከኢንፌክሽን፣ ከፀሀይ እና ከሌሎች የከባቢ አየር ንጥረ ነገሮች ይከላከላል።
ስለሆነም የቆዳ ጤናን ለመጠበቅ የትኞቹ የቆዳ እንክብካቤ ምርቶች ጥቅም ላይ እንደሚውሉ፣ ቆዳዎን እንዴት እንደሚንከባከቡ እና ምን አይነት ምርቶች በተሻለ ሁኔታ እንደሚሰሩ ብዙ የተሳሳቱ አመለካከቶች አሉ።
ቆዳዎን በሚንከባከቡበት ጊዜ ሊታሰብባቸው የሚገቡ 5 ነጥቦች አሉ፤ እነሱም፡-
1. ሰንስክሪን (የፀሐይ መከላከያዎችን) በቋሚነት መጠቀም
ለፀሐይ ብርሃን ከመጋለጥዎ 30 ደቂቃዎች በፊት የፀሐይ መከላከያዎችን (ሰን ስክሪን) በቆዳዎ ላይ ይቀቡ፤ እንደ አጠቃላይ መመሪያ መላ ሰውነትዎን ለመሸፈን 30 ግራም ሰንስክሪን ይጠቀሙ።
ሲዋኙ ከነበሩ ወይም ላብ ካለብዎ የፀሐይ መከላከያውን በድጋሜ ይጠቀሙ፤ ከቤት ውጭ ለረጅም ጊዜ ከቆዩ በየሁለት ሰዓቱ የጸሀይ መከላከያ መጠቀምን አይዘንጉ።
2. ሴራማይድ እና አልፋ ሃይድሮክሲ ንጥረ ነገር ያላቸው ውህዶች (moisturizers) መጠቀም
በእድሜ እየገፋን ስንሄድ በቆዳችን ውስጥ ያሉት የዘይት እጢዎች እንቅስቃሴ እየቀነሰ ይሄዳል፣ ስለዚህም ቆዳችን ይደርቃል፣ በቀላሉ ለቁጣ የተጋለጠ ይሆናል።
ከመታጠቢያ ከወጡ በኋላ በሶስት ደቂቃዎች ውስጥ እርጥበት መከላከያ መጠቀም ለቆዳዎ እንክብካቤ እንደሚመከር ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
3. በቂ እንቅልፍ ማግኘት
በሚያሸልቡበት ጊዜ ሰውነትዎ በቆዳው ላይ የደም ፍሰትን ይጨምራል፣ ይህም ማለት ወደ ጤናማ ሁኔታ ይነሳሉ ማለት ነው።
እንቅልፍ ማጣት በፊትዎ ላይ ባለው ቆዳ ላይ የደም ፍሰት እንዲቀንስ ያደርጋል፤ ስለዚህ በቂ እንቅልፍ ያግኙ።
4. ሲጋራ እና መሰል የትንባሆ ውጤቶችን አለመጠቀም
ትንባሆ በቆዳ ሕዋሳት ላይ ውጥረት እና የደም ስሮች መጨናነቅን ሊያስከትል ይችላል።
የደም ስሮች ለቆዳችን ደም የሚያቀርቡባቸው ቦታዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጠበቡ ይሄዳሉ፣ ይህም ለበለጠ መሸብሸብ፣ ያለጊዜው እርጅና ያስከትላል።
5. በቂ ምግብ እና ውሃ መውሰድ ናቸው።