የሀገር ውስጥ ዜና

ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ ያሸነፉት የሰላም የኖቤል ሽልማት ለሰላም ባሳዩት ቁርጠኝነት የተገኘ ነው – አቶ ገዱ አንዳርጋቸው

By Tibebu Kebede

December 17, 2019

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 1፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተርበ ዐቢይ አህመድ ያሸነፉት የሰላም የኖቤል ሽልማት ለሰላም ባሳዩት ቁርጠኝነት የተገኘ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ተናገሩ።

የጠቅላይ ሚኒስትሩን የኖቤል ሽልማት መቀበል አስመልክቶ በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ዝግጅት ተካሂዷል። በፕሮግራሙ ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ባስተላለፉት መልዕክት ይህ ሽልማት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለሰላም ባሳዩት ቁርጠኝነት የተገኘ እና እውቅናውም የመላው ኢትዮጵያውያን መሆኑን ገልጸዋል።