የሀገር ውስጥ ዜና

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ልዩ ራፖርተር የሚመራው ልዑክ የኢትዮጵያ ጉብኝት ዋና ዋና ግኝቶችን ይፋ አደረገ

By Tibebu Kebede

December 17, 2019

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 1፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በልዩ ራፖርተር ዳቪድ ካየ የሚመራው የልዑካን ቡድን ከአንድ ሳምንታት በላይ በኢትዮጵያ ከበርካታ የመንግስትና የግል ተቋማት ጋር በሚዲያና በአጠቃላይ ሀሳብን በነፃነት ከመግለፅ ጋር የተያያዙ የዴሞክራሲ መብቶች ዙሪያ ከጠቅላይ አቃቤ ህግና ሌሎች ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ሰፊ ጥናቶችን ሲያካሂድ እንደቆየ በመግለፅ ዋና ዋና ያላቸውን ግኝቶች ዛሬ ይፋ አደረገ።