የሀገር ውስጥ ዜና

እቅዶች ብልሹ አሰራርን የሚቀርፉና የዋጋ ንረትን የሚያረጋጉ መሆን አለባቸው – አቶ እንዳሻው ጣሰው

By Melaku Gedif

July 22, 2024

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው የሴክተር መስሪያ ቤቶችን የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ እየገመገሙ ነው።

አቶ እንዳሻው በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ የሁሉም ሴክተር መስሪያ ቤቶች ዕቅድ የመልካም አስተዳደር ችግርና ብልሹ አሰራርን የሚቀርፍ እንዲሁም የዋጋ ንረትን የሚያረጋጋ መሆን አለበት፡፡

የክልሉን ምርታማነት የሚያሳድግ፣ ዘላቂ ሰላም የሚያረጋግጥ እና በሁሉም መስክ ህዝብን ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆን እንዳለበትም አሳስበዋል።

የሴክተር መስሪያ ቤቶች የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ በጥልቀት ተገምግሞ ቀጣይ አቅጣጫ እንደሚቀመጥም የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡