የሀገር ውስጥ ዜና

የተመድ 4ኛው የፋይናንስ ለልማት ቅድመ ጉባዔ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ

By Feven Bishaw

July 22, 2024

 

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) 4ኛው የፋይናንስ ለልማት ቅድመ ጉባዔ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል፡፡

ጉባዔው በ5 ቀናት ቆይታው የተመድ 2030 ዘላቂ የልማት ግቦችና ከዘጠኝ ዓመት በፊት የተፈረመው የአዲስ አበባ የድርጊት መርሐ ግብር ስምምነት አፈፃፀምን እንደሚገመግም ይጠበቃል።

ጉባዔው በስፔን ከሚካሄደው 4ኛው የፋይናንስ ለልማት ዋና ጉባዔ አስቀድሞ ነው እየተካሄደ የሚገኘው።

በቅድመ ጉባዔው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ እና የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሺዴን ጨምሮ የተመድ ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች እንዲሁም የአባል ሀገራት የፋይናንስ ሚኒስትሮች እየተሳተፉ ነው።

በሳሙኤል ወርቃየሁ፣ ዙፋን ካሳሁን እና ሰዓዳ ጌታቸው