Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በጎፋ ዞን በመሬት ናዳ የተፈናቀሉትን ለመደገፍ ርብርብ ይደረጋል- አቶ ጥላሁን ከበደ

 

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን በተከሰተ የመሬት ናዳ ምክንያት የተጎዱና የተፈናቀሉትን ለመደገፍ ርብርብ እንደሚደረግ የክልሉ ርዕሰ መሥተዳድር ጥላሁን ከበደ አረጋገጡ፡፡

በተጨማሪም ለአደጋ ተጋላጭ ለሆኑ ወገኖች ተገቢው ጥንቃቄ እንዲደረግ የተቀናጀ ተግባር ይከናወናል ብለዋል፡፡

ዛሬ ረፋድ 4 ሠዓት ገደማ በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ቀበሌ በተከሰተ የመሬት ናዳ ምክንያት ለጠፋው የሰው ሕይወትም የተሰማቸውን ሐዘን ገልፀው ሕይወታቸውን ላጡ ቤተሰቦችም መፅናናትን ተመኝተዋል፡፡

በቀጣይም የተጎዱትን እና የተፈናቀሉትን ለመደገፍ፣ ለአደጋ ተጋላጭ ለሆኑም ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲደረግ የተቀናጀ ተግባር እንደሚከናወን አረጋግጠዋል፡፡

በተከሰተው አደጋ እስካሁን በተደረገ ፍለጋ ከ20 በላይ አስከሬን መገኘቱንና የሟቾች ቁጥር ሊያሻቅብ እንደሚችል የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ ምስክር ምትኩ አስታውቀዋል፡፡

የአስክሬን ፍለጋና የነፍስ አድን ሥራው ተጠናክሮ መቀጠሉንም አመላክተዋል፡፡

Exit mobile version