Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በቢሾፍቱ በዋና ዋና መንገዶችና በሰባቱ ሃይቆች ዙሪያ የኮሪደር ልማት ሥራ እየተከናወነ ነው

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በቢሾፍቱ ከተማ በዋና ዋና መንገዶችና በሰባቱም ሃይቆች ዙሪያ የኮሪደር ልማት ሥራ በ3 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር በጀት እየተከናወነ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ አስታውቋል፡፡

የአስተዳደሩ ከንቲባ አለማየሁ አሰፋ እንዳሉት÷የኮሪደር ልማቱ በከተማዋ ዘጠኝ ዋና ዋና መንገዶች በጥናት ተለይቶ ሥራው ተጀምሯል።

የኮሪደር ልማቱ ደረጃውን የጠበቀ የመንገድ ግንባታ፣ የፍሳሽ ማስወገጃና የአረንጓዴ ልማትን ጨምሮ የ3 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር በጀት ተይዞለት እየተከናወነ ይገኛል ብለዋል፡፡

በመሆኑም የኮሪደር ልማቱ በከተማዋ በሚገኙት ሰባቱም ሃይቆች ዙሪያ እየተከናወነ መሆኑን ነው ከንቲባው የገለጹት፡፡

በፕሮጀክቱ የመንገድ ማስዋብና የአረንጓዴ ልማት፣ የመናፈሻና የህጻናት መጫዎቻ ስፍራዎች እና ሌሎችም ይሰራሉ ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

Exit mobile version