የሀገር ውስጥ ዜና

218 ፍልሰተኞች ከጅቡቲ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

By Mikias Ayele

July 22, 2024

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 218 ፍልሰተኞች ከጅቡቲ ወደ ኢትዮጵያ መመለሳቸውን በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታወቀ፡፡

ኤምባሲው እና በጅቡቲ የሚገኘው የዓለም አቀፍ ፍልሰተኞች ድርጅት ጋር በመተባበር ፍልሰተኞቹ እንዲመለሱ ማድረግ መቻሉ ተመላክቷል፡፡

የጅቡቲ-የመን መንገድ እጅግ አደገኛ ከመሆኑም በላይ በየቀኑ የብዙዎችን ህይወት እያሳጣን እንደሚገኝ የጠቆመው ኤምባሲው ዜጎች ራሳቸውን እና ቤተሰባቸውን ከህገ ወጥ ፍልሰት እንዲጠብቁ ጥሪ አቅርቧል፡፡