አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የዜጎች እኩል ተሳትፎና ተጠቃሚነት የተረጋገጠባትና የማህበራዊ ጥበቃ አገልግሎቶች የተስፋፉባትን ኢትዮጵያ ዕውን እናደርጋለን ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ፡፡
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የሥራ ሃላፊዎች ጋር ውይይት አድርገናል ብለዋል፡፡
በውይይቱም በተሰሩ ዋና ዋና ሥራዎች እና በቀጣይ ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ዙሪያ በዝርዝር ምክክር መደረጉን ገልፀዋል፡፡
የዜጎች እኩል ተሳትፎና ተጠቃሚነት የተረጋገጠባትና የማህበራዊ ጥበቃ አገልግሎቶች የተስፋፉባትን ኢትዮጵያ ዕውን እናደርጋለን ሲሉም አስገንዝበዋል፡፡