አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የ2017 በጀት ዓመት 17 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር ሆኖ ጸደቀ።
የቀረበው በጀት ከክልል ገቢ የሚሰበሰብ፣ ከፌዴራል መንግስት ድጎማና ከሌሎች የገቢ ምንጮች የሚገኝ መሆኑን ተገልጿል።
በዚህም መሠረት ለክልል ማዕከል መ/ቤቶች መደበኛና የካፒታል ወጪ 1 ነጥብ 5 ቢሊየን፣ ለዞኖች ጥቅል በጀት 14 ነጥብ 5 ቢሊየን፣ ለክልላዊ ፕሮግራሞች 995 ነጥብ 6 ሚሊየን፣ ለዘላቂ ልማት ግቦች ማስፈፀሚያ 434 ነጥብ 7 ሚሊየን፣ ለክልሉ መጠባበቂያ በጀት 120 ሚሊየን በአጠቃላይ 17 ቢሊየን 622 ሚሊየን 88 ሺህ 402 ብር ሆኖ መጽደቁን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ አመላክቷል።