Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የፌዴሬሽን ምክር ቤት በጎፋ ዞን በመሬት መንሸራተት አደጋ በደረሰው ጉዳት የተሰማውን ሀዘን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌዴሬሽን ምክር ቤት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ በኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ የተከሰተውን ድንገተኛ የመሬት መንሸራተት አደጋ ተከትሎ በደረሰው የሰው ህይወት መጥፋት የተሰማውን ሀዘን ገለጸ፡፡

ምክር ቤቱ የተከሰተውን የመሬት ንሸራተት አደጋ ተከትሎ በዜጎች ላይ በደረሰው አደጋ የተሰማውን እጅግ ጥልቅና ልባዊ ሀዘን በመግለጽ በአደጋው ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸውን ዜጎች መልሶ ለማቋቋም ከክልሉ መንግስትና ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር በመሆን የበኩሉን አስተዋጽኦ እንደሚያደርግም አረጋግጧል።

ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች በሙሉ መፅናናትን እና ብርታትን እንደሚመኝ መግለጹንም የምክር ቤቱ መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version