Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በጎፋ ዞን በደረሰ የመሬት ናዳ ህይወታቸውን ላጡ ወገኖች የተሰማቸውን ሀዘን ገለፁ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ በኬንቾ ቀበሌ በደረሰ የመሬት ናዳ ህይወታቸውን ላጡ ወገኖች የተሰማቸውን ሀዘን ገልፀዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው÷”በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ ድንገተኛ የመሬት ናዳ አደጋ የበርካታ ዜጎቻችንን ሕይወት ቀጥፏል” ብለዋል።

“በደረሰው አስከፊ ጉዳት የተሰማኝን ጥልቅ ሀዘን እገልጻለሁ” ነው ያሉት።

አደጋውን ተከትሎ የፌዴራል የአደጋ መከላከል ግብረ-ሀይል በአካባቢው ተሰማርቶ የአደጋውን ጉዳት ለመቀነስ ርብርብ እያደረገ መሆኑንም ገልፀዋል፡፡

Exit mobile version