የሀገር ውስጥ ዜና

በመሬት ናዳ ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸውን ዜጎች መልሶ ለማቋቋም መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል- ም/ጠ/ሚ ተመስገን ጥሩነህ

By Shambel Mihret

July 23, 2024

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በተከሰተው የመሬት ናዳ ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸውን ዜጎቻችንን መልሶ ለማቋቋም ፤የጉዳቱን ሰለባዎች ለመርዳት መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ ያደርጋል ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለፁ፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን በደረሰው የመሬት ናዳ ህይወታቸውን ላጡ ወገኖች የተሰማቸውን ሀዘን ገልፀው በአደጋው ጉዳት ለደረሰባቸው የተጎጂ ቤተሰቦች እና ዘመድ ወዳጆች መፅናናትን ተመኝተዋል፡፡

በቀጣይም በአደጋው ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸውን ዜጎቻችንን መልሶ ለማቋቋም የጉዳቱን ሰለባዎች ለመርዳት መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል፡፡