Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በክልሉ የትምህርት ስብራትን ለመጠገን በተከናወነ ሥራ ተጨባጭ ለውጥ መታየቱ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የትምህርት ጥራትን ለማሻሻልና ስብራቱን ለመጠገን በተከናወኑ ተግባራት ተጨባጭ ለውጦች እየታዩ መሆኑን ርዕሰ መሥተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር ኢ/ር) ገለጹ፡፡

የክልሉ ትምህርት ቢሮ “የተማረ ትውልድ ለሁለንተናዊ ብልጽግና” በሚል መሪ ሐሳብ የ2017 የትምህርት ዘመን የዝግጅት ምዕራፍ ሥራዎች የንቅናቄ መድረክ በታርጫ ከተማ አካሂዷል፡፡

ርዕሰ መሥተዳድሩ በመድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ በክልሉ የትምህርት ጥራትን ለማሻሻልና የትምህርት ዘርፍ ስብራትን ለመጠገን በተከናወኑ ተግባራት ተጨባጭ ለውጦች እየታዩ ነው ብለዋል፡፡

የሕብረተሰብ ተሳትፎ ለትምህርት ዘርፍ ልማት ያለው አስተዋጽኦ ከፍተኛ በመሆኑ ድጋፉ እንዲጠናከር ጠይቀዋል፡፡

በዘርፉ የባለድርሻ አካላት አስተባባሪነትና በሕብረተሰቡ የነቃ ተሳትፎ የመማሪያና ማስተማሪያ መጽሐፍትን ለማሳተም እየተሠራ ነው ማለታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡

የመምህራንን አቅም ለማጎልበትና መሠረታዊ ጥያቄዎችን ለመፍታትም የክልሉ መንግስት ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ እንደሚገኝም አስታውቀዋል፡፡

Exit mobile version