አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኮይሻ ጊቤ 4 የኃይል ማመንጫ ግድብ ከስድስት ወራት በፊት ከነበረው ግምገማችን በኋላ ትርጉም ያለው እድገት አሳይቷል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ ለ14ኛ ጊዜ በፕሮጀክቱ ሥፍራ ተገኝተው የሥራ ሂደቱን መገምገማቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡
በሺህዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች በፕሮጀክቱ ቀን እና ሌሊት በፈረቃ በትጋት እየሠሩ እንደሚገኙም ተገልጿል፡፡
ከስድስት ወራት በፊት ከነበረው ግምገማ በኋላም ትርጉም ያለው እድገት መኖሩን ተመልክቻለሁ ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡
የኮይሻ ጊቤ 4 የኃይል ማመንጫ ግድብ ከታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ቀጥሎ ትልቁ መሆኑም ተጠቅሷል፡፡