የሀገር ውስጥ ዜና

የኬንያ ፕሬዚዳንት በመሬት መንሸራተት ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖች የተሰማቸውን ሐዘን ገለጹ

By Mikias Ayele

July 27, 2024

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኬንያ ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በተከሰተ የመሬት መንሸራተት አደጋ ሕይወታቸውን ላጡ ሰዎች የተሰማቸውን ሐዘን ገለጹ፡፡

ፕሬዚዳንቱ ባስተላለፉት ሐዘን መግለጫ መልዕክት÷ በአደጋው ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖች በኬንያ መንግሥት እና ሕዝብ ስም የተሰማቸውን ሐዘን ገልጸዋል፡፡

ለሟች ቤተሰቦች እና ጉዳት ለደረሰባቸው ሰዎች መጽናናትን ተመኝተው÷ ኬንያ ከኢትዮጵያ መንግሥትና ሕዝብ ጎን መሆኗን አረጋግጣለሁ ብለዋል፡፡