አዲስ አበባ፣ ሕዳር 11፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የቱርኩ ፕሬዚዳንት ሬሲፕ ጣይፕ ኤርዶኻን ሀገራቸው ዩክሬን ሩሲያን በሚሳኤል እንድትመታ አሜሪካ የሰጠችውን ፈቃድ እውቅና እንደማትሰጥ አስታወቁ፡፡
ፕሬዚዳንቱ ይህ የአሜሪካ ድርጊት ዓለምን ወደ አዲስ እና ከፍተኛ ጦርነት የሚመራ ነው ብለዋል፡፡
ይህ በሞስኮ ላይ የሚደረገው የምዕራባውያን ጫና ጦርነቱ አድማሱን በማስፋት እንዲባባስ ሊያደርገው እንደሚችል ገልጸው÷ የአሜሪካን ድርጊት መኮነናቸውን ስፑትኒክ አፍሪካ ዘግቧል፡፡
የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ከቀናት በፊት ዩክሬን አሜሪካ ያቀረበችላትን የረጅም ርቀት ተወንጫፊ ሚሳኤል ሩሲያን ለመምታት እንድትጠቀም ፈቃድ መስጠታቸው ይታወሳል፡፡