አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ18ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የበዓል ሰሞን (ቦክሲንግ ደይ) መርሐ-ግብር ዛሬ ሁለት ጨዋታዎች ይደረጋሉ፡፡
በመርሐ-ግብሩ መሠረት ምሽት 4 ሠዓት ከ30 ላይ ብራይተን ከብሬንትፎርድ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡
እንዲሁም ምሽት 5 ከ15 አርሰናል ኤሚሬትስ ስታዲዬም ላይ አዲስ አዳጊውን ኢፕስዊች ታውን ይገጥማል፡፡
ትናንት በተደረጉ ጨዋታዎች ሊቨርፑል ሌስተር ሲቲን 3 ለ 1 በማሸነፍ አንድ ቀሪ ጨዋታ እየቀረው መሪነቱን በማጠናከር ከተከታዩ ያለውን የነጥብ ልዩነት በሰባት ማስፋት ችሏል፡፡
እንዲሁም ፉልሃም ቼልሲን 2 ለ1፣ ኖቲንግሃም ፎረስት ቶተንሃም ሆትስፐርን 1 ለ 0፣ ኒውካስል ዩናይትድ አስቶንቪላን 3 ለ 0፣ ዎልቭስ ማንቼስተር ዩናይትድን 2 ለ 0፣ ዌስትሃም ዩናይትድ ሳውዝሃምፕተንን 1 ለ 0 አሸንፈዋል፡፡
ማንቼስተር ሲቲ ከኤቨርተን 1 ለ 1 እንዲሁም ቦርንማውዝ እና ክሪስታል ፓላስ ያለምንም ግብ አቻ ተለያይተዋል፡፡