የሀገር ውስጥ ዜና

ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ የጎንደር አብያተ መንግሥታት እድሳትን ጎበኙ

By amele Demisew

January 18, 2025

አዲስ አበባ፣ ጥር 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ በዳግማዊ አጼ ቴዎድሮስ መታሰቢያ ሃውልት ላይ ተገኝተው “የዘመናዊቷ ኢትዮጵያ አባት” ሲሉ የአበባ ጉንጉን አስቀምጠዋል።

የጥምቀት በዓልን በጎንደር ለመታደም ወደ ታሪካዊቷ ጎንደር ያቀኑት ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር በጎንደር የፋሲል አብያተ መንግሥታት እድሳት እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን መጎብኘታቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡