አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአውሮፓ የተለያዩ ከተሞች የሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታዎች ምሽት ላይ ሲደረጉ ቤኔፊካ ከባርሴሎና እንዲሁም አትሌቲኮ ማድሪድ ከባየርሊቨርጉሰን የሚያደርጉት ፍልሚያ ይጠበቃል፡፡
ምሽት 2 ከ45 ላይ ቤርጋሞ ላይ አታላንታ ከስትሩም ግራዝ እንዲሁም ሞናኮ ከአስቶንቪላ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡
ምሽት 5 ሠዓት ላይ ደግሞ አትሌቲኮ ማድሪድ ከባየርሊቨርጉሰን፣ ቤኔፊካ ከባርሴሎና፣ ቦሎኛ ከቦሩሺያ ዶርቱመንድ፣ ክለብ ብሩጅ ከጁቬንቱስ፣ ሊቨርፑል ከሊል፣ ሬድ ስታር ቤልግሬድ ከፒኤስቪ እንዲሁም ስሎቫን ብራቲስላቫ ከስቱትጋርት ይጫወታሉ፡፡