የሀገር ውስጥ ዜና

የሸኮ ብሔር ዘመን መለወጫ በዓል” ቲከሻ ቤንጊ” እየተከበረ ነው

By amele Demisew

January 23, 2025

አዲስ አበባ፣ ጥር 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሸኮ ብሔር ዘመን መለወጫና የምስጋና በዓል “ቲከሻ ቤንጊ” በቴፒ ከተማ እየተከበረ ነው።

ቲከሻ ቤንጊ የተዘራው እህል ከተፈጥሮ አደጋ ተጠብቆ በመድረሱ፣ የተሰቀለው ቀፎ ምርት በመስጠቱና በአካባቢው ሰላም በመስፈኑ ለፈጣሪ ምስጋና የሚቀርብበት በዓል ነው።

በበዓሉ ከደረሰው እህል በየአይነቱ ቀርቦ በባላባቶች ይቀመሳል ፤ለአካባቢው ነዋሪዎችም ይዳረሳል።

የቲከሻ ቤንጊ በዓል በተለያዩ ምክንያቶች ሳይከበር ተቋርጦ ከቆየ በኋላ በዘንድሮው አመት ለሁለተኛ ጊዜ እየተከበረ እንደሚገኝ ተመላክቷል።

በተስፋዬ ምሬሳ