ፋና ስብስብ

አንዲት በግ አምስት ግልገሎችን ወለደች

By Feven Bishaw

January 24, 2025

አዲስ አበባ፣ ጥር 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በምስራቅ ጎጃም ዞን በደብረ ወርቅ ከተማ አንዲት በግ 5 ግልገሎችን ወልዳለች።

 

የተወለዱት ግልገሎች ሁለቱ ወንዶች ሲሆን ሶስቱ  ሴቶች ናቸው፡፡

 

በጓ ከዚህ በፊትም በአንድ ጊዜ ሶስት እና አራት ግልገሎችን ወልዳ እንደነበር የበጓ ባለንብረት ተናግረዋል።

 

በጓ እና ግልገሎቿም በአሁኑ ሰዓት በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኙ የእናርጅ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡