Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ፕሬዚዳንት ፑቲን ከፕሬዚዳንት ትራምፕ ጋር ለመወያየት ዝግጁ መሆናቸውን ክሬምሊን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከአሜሪካ አቻቸው ዶናልድ ትራምፕ ጋር የስልክ ውይይት ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን ክሬምሊን አስታወቀ፡፡

የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ ሩሲያ ከትራምፕ ጋር ለሚደረገው ውይይት የዋሽንግተንን ምላሽ እየጠበቀች መሆኗን ገልጸዋል፡፡

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሩሲያ ከዩክሬይን ጋር የምታደርገውን ጦርነት በፍጥነት ለማስቆም እና የኒዩክሌር መሳሪያ ቅነሳን በተመለከተ ከፑቲን ጋር መነጋገር እንደሚፈልጉ መግለጻቸው ይታወሳል፡፡

ይህንን ተከትሎ ክሬምሊን ውይይቱን ፕሬዚዳንት ፑቲንም ይፈልጉታል ማለቱን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

በዚህ ሳምንት መጨረሻ ውይይቱ ይካሄድ እንደሆነ ለቀረበላቸው ጥያቄ ፔስኮቭ በሰጡት ምላሽ “ጥልቅ ውይይት ለማድረግ ፊት ለፊት ከመገናኘታችን በፊት የስልክ ውይይቱን በማንኛውም ጊዜ ለማድረግ እኛ ዝግጁ ነን፤ አሁን የዋሽንግተንን ምላሽ በመጠበቅ ላይ እንገኛለን” ብለዋል።

Exit mobile version