Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ፖሊስ መጣልን እንጂ መጣብን እንዳይባል መስራት ይገባል – ኮሚሽነሩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) “ፖሊስ እንኳን መጣልን እንጂ ለምን መጣብን እንዳይባል ሁሉንም ዜጎች በዕኩልነት ማገልገል ይገባል” ሲሉ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል ገለጹ፡፡

ኮሚሽነር ጀነራሉ ለ6ኛ ዙር ከኢንስፔክተር ወደ ዋና ኢንስፔክተር የተሸጋገሩ የፌደራል፣ የድሬዳዋ፣ የአዲስ አበባ፣ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ፣የደቡብ ኢትዮጵያ እና የሲዳማ ክልል ፖሊስ መኮንኖችን አስመርቀዋል።

ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል በዚህ ወቅት÷ የኢትዮጵያ ፖሊስ ላለፉት ስድስት ዓመታት የለውጡ መንግስት በሰጠው ከፍተኛ ትኩረት በማንሰራራት ላይ ያለ ተቋም ነው ብለዋል፡፡

ሪፎርሙ በፌደራል ፖሊስ ብቻ የቆመ ሳይሆን አጠቃላይ የሀገሪቱን የፖሊስ ተቋማት ለማዘመንና በተቻለ መጠን ደረጃውን በጠበቀ መልኩ እንዲያድጉና እንዲዘምኑ ለማድረግ የፌደራል ፖሊስ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ እንደሚገኝም መግለጻቸውን ከፌዴራል ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ኮሚሽነር ጀነራሉ” ህብረተሰቡ ፖሊስ እንኳን መጣልን እንጂ ለምን መጣብን እንዳይል ሁሉንም ዜጎች በዕኩልነት ማገልገል አለባችሁ” ሲሉም ለተመራቂዎቹ አስገንዝበዋል፡፡

Exit mobile version