Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የፍትህና የዳኝነት ስርዓቱን ለማዘመን የሚያስችል የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የፍትህና የዳኝነት ስርዓቱን ዘመናዊና ቀልጣፋ ለማድረግ የሚያስችል የምክክር መድረክ በደብረ ብርሃን ከተማ መካሄድ ጀምሯል፡፡

የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አለምአንተ አግደው በዚህ ወቅት÷ ነጻና ጠንካራ የፍትህ ተቋማትን በመገንባት ለፍትህ ጠያቂው የተፋጠነ ፍትህ ማቅረብ ይጠበቃል ብለዋል፡፡

ፍትህ በአንድ ተቋም ተጀምሮ በአንድ ተቋም የሚያልቅ ባለመሆኑ የትብብር መድረኩ አባል ተቋማት ፍርድ ቤቶች፣ፖሊስ እና ማረሚያ ቤቶች በጋራ አቅደው የተቀላጠፈ ቅንጅታዊ አሰራሮችን ሊያጠናክሩ እንደሚገባም አንስተዋል፡፡

መልካም አስተዳደርን ለማስፈን፣የዜጎችን ሰብዓዊ መብትና ነጻነት ለማስጠበቅ ቁልፍ በተባሉት የፍትህ ተቋማት የማሻሻያ ስራዎች ተግባራዊ በመደረጋቸው ለውጦች ታይተዋል ያሉት አቶ አለምአንተ አሰራሩን በቴክኖሎጂ ለማስደገፍ ክልሉ ጅምር እንቅስቃሴ ላይ ነው ሲሉም ተናግረዋል፡፡

በዳኝነትና የፍትህ አካላት የትብብር መድረኩ ላይ የክልል የፍትህ አካላት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ የዞን አመራሮች፣ የፍርድ ቤት ዳኞችና ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ነው፡፡

በታለ ማሞ

Exit mobile version