ስፓርት

 ኢትዮ ኤሌክትሪክ እና ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ አሸነፉ

By Mikias Ayele

January 26, 2025

አዲስ አበባ፣ ጥር 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 16ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ኢትዮ ኤሌክትሪክ እና ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸነፉ።

ምሽት 12:00 ሰዓት ላይ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው የኢትዮ ኤሌክትሪክ እና ሲዳማ ቡና ጨዋታ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከእረፍት በፊት ናትናኤል ገ/ጊዮርጊስ ባስቆጠራቸው ግቦች 2 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

ቀን 9:00 ሰዓት ላይ በተካሄደው የሊጉ ጨዋታ ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ሀድያ ሆሳዕናን ቡልቻ ሹራ ባስቆጠራት ግብ 1 ለ 0 በማሸነፍ ሶስት ነጥብ ይዞ ወጥቷል።