ስፓርት

ቅዱስ ጊዮርጊስ ወላይታ ድቻን አሸነፈ

By Mikias Ayele

January 29, 2025

አዲስ አበባ፣ ጥር 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 17ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ቅዱስ ጊዮርጊስ ወላይታ ድቻን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

ቀን 9 ሰዓት በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደ ጨዋታ አብዱ ሳሚዮ እና አማኑኤ ኤርቦ የቅዱስ ጊዮርጊስ ግቦችን አስቆጥረዋል፡፡

ውጤቱን ተከትሎም ፈረሰኞቹ ነጥባቸውን ወደ 28 ከፍ አድርገዋል።

የ17ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ቀጥሎ ሲካሄድ ምሽት 12 ሰዓት ባህርዳር ከተማ ከኢትዮጵያ ቡና ጋር ይጫወታል።