Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የአይኤምኤፍ ማኔጅንግ ዳይሬክተር ኢትዮጵያን ሊጎበኙ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 22፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) ማኔጅንግ ዳይሬክተር ክሪስታሊና ጆርጂዬቫ በኢትዮጵያ ለሁለት ቀናት ይፋዊ የሥራ ጉብኝት እንደሚያደርጉ የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ።

ማኔጂንግ ዳይሬክተሯ በጉብኝታቸው ከመንግስት ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ጋር በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እይታ፣ ፖሊሲው ቅድሚያ በሚሰጣቸው ጉዳዮች እና እየተካሄዱ ባሉ የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች ላይ እንደሚመክሩ ይጠበቃል፡፡

በተጨማሪም ከግሉ ዘርፍ ተወካዮች ጋር በኢትዮጵያ ስላለው የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ እና የገበያ እድሎች እንደሚወያዩ ተመላክቷል፡፡

ክሪስታሊና ጆርጂዬቫ በኢትዮጵያ የሚያደርጉት ጉብኝት በማኔጂንግ ዳይሬክተርነት ከተመረጡ ወዲህ የመጀመሪያቸው እንደሚሆን የገንዘብ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡

ጉብኝቱ አይኤምኤፍ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ልማት ለመደገፍ እና የጋራ ዘላቂ ብልጽግናን ለማረጋገጥ በፖሊሲዎች ላይ ውይይት ለማድረግ ያለውን ቁርጠኝነት ያረጋገጠበት መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

Exit mobile version