Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ፍልስጤማውያን ግዛታቸውን ለማንም አሳልፈው አይሰጡም- መሃሙድ አባስ

አዲስ አበባ፣ ጥር 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ፍልስጤማውያን ስለ ግዛታቸው ተስፋ አይቆርጡም ሲሉ የፍልስጤም ፕሬዚዳንት መሃሙድ አባስ ገለጹ፡፡

መሃሙድ አባስ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ÷ዩናይትድ ስቴትስ ጋዛ ሰርጥን በጊዜያዊነት በመቆጣጠር መልሳ መገንባት ትፈልጋለች ማለታቸውን ተከትሎ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

በምላሻቸውም “ለበርካታ ዘመናት የተዋጋንለትን የፍልስጤምና የፍልስጤማውያን ነፃነት እንዲጣስ አንፈቅድም” ብለዋል፡፡

ትራምፕ ፍልስጤማውያን ወደ ሌላ ቦታ እንዲዛወሩ ያቀረቡት ሃሳብ ዓለም አቀፍ ሕግን  የጣሰ መሆኑን ጠቁመው÷ፍልስጤማውያን ስለ መሬታቸው ተስፋ እንደማይቆርጡ አስገንዝበዋል፡፡

ፍልስጤማውያን ግዛታቸውን ለማንም አሳልፈው አይሰጡም ያሉት ፕሬዚዳንቱ÷ የትራምፕን ሃሳብም ተቀባይነት የሌለው ሲሉ አጣጥለዋል፡፡

አሜሪካ ጋዛ ሰርጥን በጊዜያዊነት ለመቆጣጠር ያቀረቡትን ሃሳብ በርካታ ሀገራትን ጨምሮ አምባሳደሮች እና ሌሎች ዲፕሎማቶች እየተቃወሙት እንደሚገኙ የዘገበው ጂኦ ፖለቲክስ ነው፡፡

Exit mobile version