አዲስ አበባ፣ ጥር 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የዓለም ጤና ድርጅት ለኢትዮጵያ የውሃ ጥራት መመርመሪያ ኪቶችን ድጋፍ አድርጓል፡፡
የጤና ሚኒስትር ዴዔታ ዶ/ር ደረጄ ዱጉማ በርክክቡ ወቅት እንዳሉት÷ የውሃ ጥራት መመርመሪያ መሳሪያዎቹ የውሃ ብክለትን ቀድመው በመለየት ኮሌራን ጨምሮ የውሃ ወለድ በሽታዎችን ለመቀነስ ያስችላሉ፡፡
ኪቶቹ 23 የኮሌራና ሌሎች የአደጋ ጊዜ ተጠቂ ወረዳዎችን በመለየት እንደሚሰራጩ ጠቁመው÷በሁሉም ክልሎች በአማካይ እስከ 7 ሚሊየን ለሚሆኑ ዜጎች አገልግሎት መስጠት ያስችላሉ ብለዋል።
የፍተሻ ኪቶች የክልል ጤና ቢሮዎችና የወረዳ ጤና ጽ/ቤቶችን የውሃ ጥራት ክትትል አቅም ለማሳደግ ሚናቸው ጉልህ ነው መባሉን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡