አዲስ አበባ፣ ጥር 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት በቴክኖሎጂ ልማት ዘርፍ ለወጣቶች የሥራ ዕድል ሊፈጥሩ የሚያስችሉ የተለያዩ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን እየሰራ እንደሚገኝ አስታወቀ።
በኢንስቲትዩቱ የተሰሩ አምስት የፕላዝማ እና ራውተር ሲ ኤን ሲ ማሽኖችን ለአማራ፣ ትግራይ፣ ሲዳማ፣ አፋር እና ቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልሎች አስረክቧል።
የፕላዝማ ሲ ኤን ሲ ማሽን በጨረር ብረቶችን በተለያየ ቅርጽ መቁረጥ የሚያስችል እንደሆነ የኢኒስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አብዲሳ ይልማ ገልጸዋል፡፡
የራውተር ሲ ኤን ሲ ማሽን ደግሞ በእንጨቶች ላይ የተለያዩ ቅርጾችን ለማውጣት ያስችላል።
በቀጣይም የቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲኖር በማድረግ ወጣቶች በተሰራላቸው ማሽን መስራት ብቻ ሳይሆን ማሽኑንም መስራት እንዲችሉ ይደረጋልም ብለዋል።
በዘመን በየነ