አዲስ አበባ፣ ጥር 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ብራዚላዊው የቀድሞው የሪያል ማድሪድ ተከላካይ ማርሴሎ ከእግር ኳስ ራሱን ማግለሉን አስታወቀ፡፡
የግራ መስመር ተከላካዩ ማርሴሎ በሪያል ማድሪድ ቤት ስኬታማ ጊዜን ያሳለፈ ሲሆን 5 የሻምፒዮንስ ሊግ እና 6 የላሊጋ ዋንጫዎችን ከሎስ ብላንኮቹ ጋር ማንሳት ችሏል፡፡
ለብራዚል ብሔራዊ ቡድን ደግሞ 58 ጊዜ ተሰልፎ በመጫዎት 6 ጎሎችን በስሙ አስመዝግቧል፡፡
ከሪያል ማድሪድ በመውጣት በግሪኩ ኦሎምፒኮስ እና በብራዚሉ ፉለሉሜንሴ ያልተሳካ ጊዜያት ያሳለፈው ማርሴሎ ከደቂቃዎች በፊት በለቀቀው ተንቀሳቃሽ ምስል በይፋ ጫማ መስቀሉን አስታውቋል፡፡