Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ጃፓን ለኢትዮጵያ የ1 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር ድጋፍ አደረገች

አዲስ አበባ፣ ጥር 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ጃፓን ለኢትዮጵያ የ1 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር ድጋፍ አድርጋለች፡፡

ድጋፉ ከተባበሩት መንግስታት ኤጀንሲዎች እና ከዓለም አቀፍ ፈንድ ጋር በመተባበር የተደረገ መሆኑን በኢትዮጵያ የጃፓን ኤምባሲ አስታውቋል፡፡

የተደረገው ድጋፍ ለተለያዩ የልማት ሥራዎች እና ለሰብዓዊ እርዳታ እንደሚውል ነው የተገለጸው፡፡

ጃፓን በተለያዩ ዘርፎች ለኢትዮጵያ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥልም ኤምባሲው ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን የላከው መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version