Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በኦሮሚያ ክልል 327 ሚሊየን ኩንታል ምርት ተሰበሰበ

አዲስ አበባ፣ ጥር 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኦሮሚያ ክልል በ2016/17 ምርት ዘመን እስካሁን 327 ሚሊየን ኩንታል ምርት መሰብሰቡን የኦሮሚያ ክልል ኮሚኒኬሽን ቢሮ አስታወቀ።

የቢሮው ም/ሃላፊ እሸቱ ሲርኔሳ በሰጡት መግለጫ÷በኦሮሚያ ክልል ባለፉት 6 ወራት በተለያዩ ዘርፎች ላይ በተከናወነ ሥራ አበረታች ውጤት መመዝገቡን ተናግረዋል፡፡

በምግብ ራስን ለመቻል፣ ወደ ውጪ የሚላክን ምርት ለማሳደግ፣ ተኪ ምርትን ለመጨመርና የሥራ እድል ለመፍጠር በገጠርና በከተማ ግብርና ላይ በትኩረት መስራቱን አንስተዋል፡፡

በክልሉ በክረምት እርሻ 11 ነጥብ 6 ሚሊየን ሄክታር መሬት በዘር በመሸፈን እስካሁን 327 ሚሊየን ኩንታል ምርት መሰብሰቡን ገልጸዋል፡፡

በሌላ በኩል በክልሉ ሰላም እንዲሰፍን ከታጣቂዎች ጋር የሰላም ስምምነት መደረጉ ውጤት የታየበት መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

በታሪኩ ለገሰ

Exit mobile version