አዲስ አበባ፣ ጥር 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) 10ኛዉ የህብረተሰብ ጤና አደጋዎች ቁጥጥር ፎረም በሀዋሳ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡
ፎረሙ “የማይበገር የህብረተሰብ ጤና አደጋ ቁጥጥር ለብሔራዊ ጤና ደህንነት” በሚል መሪ ሃሳብ ነው እየተካሄደ የሚገኘው፡፡
በፎረሙ የጤና ሚኒስትር ዴኤታ አየለ ተሾመ ፣የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዳይሬክተሮች፣ የክልል ባለድርሻ አካላት እና አጋር ድርጅቶች እየተሳተፉ ነው።
አቶ አየለ ተሾመ በዚህ ወቅት ÷ በአዲሱ የጤና ፖሊሲ ድንገተኛ አደጋዎችና ወረርሽኞችን የመከላከል ስራ መጠናከር እንዳለበት ጠቁመው ፤የፀረ ተህዋስያን ህክምና ባህልም አብሮ ማደግ ይገባዋል ብለዋል።
የኢትዮጵያ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር መሳይ ሀይሉ በበኩላቸው÷በሀገሪቱ የተከሰቱ ድንገተኛ አደጋዎች ላይ የተቀናጀ ስራ በመሠራቱ ሊደርስ የሚችለውን አደጋ መቀነስ እንደተቻለ ተናግረዋል።
በተለይ የወባ ወረርሽኝን ለመከላከል በተሰራው ስራ 52 ነጥብ 8 ከመቶ መቀነስ መቻሉን አንስተዋል።
በመቅደስ አስፋውና ደብሪቱ በዛብህ