የሀገር ውስጥ ዜና

የመደመር መንገድ ወደ ብልጽግና ግብ ለመድረስ እጅግ የተሻለው መንገድ ነው – ም/ጠ/ሚ ተመስገን

By amele Demisew

February 07, 2025

አዲስ አበባ፣ ጥር 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የመደመር መንገድ ወደ ብልጽግና ግብ ለመድረስ እጅግ የተሻለው መንገድ ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክ ÷”የኢትዮጵያ የትናንት እና የዛሬ ጸጋዎች ከእኛ ጥረት ጋር ሲደመሩ፣ ውጤታቸው ከድምሩ በላይ ነው፤እርሱም ሁለንታዊ ብልጽግና ነው” ብለዋል።

የመደመር መንገድ ወደ ብልጽግና ግብ ለመድረስ እጅግ የተሻለው መንገድ ነው ሲሉም አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡