Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በድሮን ታክቲካል አጠቃቀም የሰለጠኑ የፖሊስ እና የሪፐብሊካን ጋርድ አባላት ተመረቁ

አዲስ አበባ፣ ጥር 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ፌደራል ፖሊስ በድሮን ታክቲካል አጠቃቀም ያሰለጠናቸውን የፖሊስ እና የሪፐብሊካን ጋርድ የድሮን ባለሙያዎች አስመርቋል፡፡

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል በዚህ ወቅት÷ ስልጠናው የፖሊስ መኮንኖች ሙያዊ ኃላፊነታቸውን ለመወጣት ያላቸውን አቅም እንደሚያጠናክር ገልጸዋል፡፡

ስልጠናውን ጨርሰው የተመረቁ የፌደራል ፖሊስ እና የሪፐብሊካን ጋርድ የድሮን ባለሙያዎች በስልጠናው ያገኙትን እውቀት ለተፈለገው አላማ ብቻ እንዲያውሉም መክረዋል፡፡

የተባበሩት ዐረብ ኢምሬቶች የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር እና የዱባይ ፖሊስ ስልጠናው ስኬታማ እንዲሆን ላደረጉት ሙያዊና የሎጂስቲክስ ድጋፍም ኮሚሽነር ጄነራሉ ምስጋና ማቅረባቸውን ከፌዴራል ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል ፡፡

“በድጋፍ የተሰጡን ዘመናዊ ተሽከርካሪዎች፣ ድሮኖች እና ሞተር ሳይክሎች የሥራ ቅልጥፍና እና ምላሽ ሰጪነታችንን በእጅጉ ያሳድጉልናል” ሲሉም ነው የገለጹት፡፡

Exit mobile version