Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በብራዚል አነስተኛ አውሮፕላን አውቶብስ ላይ ተከስክሳ የ2 ሰዎች ሕይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ጥር 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በብራዚል ሳዖ ፖሎ ከተማ አነስተኛ አውሮፕላን በህዝብ ማመላላሻ ተሽከርካሪ ላይ ተከስክሳ የሁለት ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተሰምቷል፡፡

በትራፊክ በምትጨናነቀው የብራዚሏ ግዙፏ ከተማ ሳዖ ፖሎ አውሮፕላኗ በህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ላይ ተከስክሳ በእሳት መያያዟ ተገልጿል።

በአደጋው ከሞቱት በተጨማሪ በህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ውስጥ የነበሩ ሰዎችን ጨምሮ አንድ ሞተረኛ ጉዳት ደርሶባቸው ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸው ተመላክቷል፡፡

ሕይወታቸው ያለፉት ሁለቱ ሰዎች ግን በአውሮፕላኗ ውስጥ የነበሩ መሆናቸውን የዘገበው ቢቢሲ ነው፡፡

Exit mobile version