አዲስ አበባ፣ ጥር 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ዛሬ በተጀመረው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 19ኛ ሳምንት መርኃ ግብር ጨዋታ ስሑል ሽረ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲንን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸነፈ።
ምሽት 12፡00 ላይ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው በዚህ ጨዋታ ለስሑል ሽረ የማሸነፊያውን ግብ በ25ኛው ደቂቃ ያስቆጠረው ኤልያስ አህመድ ነው።
ቀደም ብሎ 9፡00 ላይ አዳማ ከተማ ከሲዳማ ቡና ያደረጉት ጨዋታ 1 ለ 1 በሆነ ውጤት መጠናቀቁ ይታወሳል።
የሊጉን የደረጃ ሰንጠረዥ ኢትዮጵያ መድህን በ16 ጨዋታዎች በ32 ነጥብ ሲመራ ቅዱስ ጊዮርጊስ በ29 ሁለተኛ፣ መቻልና ሃድያ ሆሳዕና በእኩል ነጥብ በግብ ክፍያ ተበላልጠው በቅደም ተከተል ሶስተኛ እና አራተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።
ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ 17 ጨዋታ ተጫውቶ በ7 ነጥብ በሊጉ መጨረሻ ደረጃን ሲይዝ ሃዋሳ ከተማ በ15 ነጥብ 17ኛ እንዲሁም ስሑል ሽረ በእኩል 15 ነጥቦች 16ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።