አዲስ አበባ፣ የካቲት 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በፈረንሳይ ሜዝ በተካሄደ የ800 ሜትር የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና ውድድር እትሌት ፅጌ ድጉማ አሸንፋለች፡፡
ፅጌ የ800 ሜትሩን 1 ደቂቃ ከ58 ሴኮንድ ከ97 ማይክሮ ሴኮንድ በመጨረስ በቀዳሚነት ማጠናቀቋን የዓለም አትሌቲክስ መረጃ ያመላክታል፡፡
ፅጌ ያስመዘገበችው የ800 ሜትር የቦታው ክብረ-ወሰን ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
በሴቶች የ1 ሺህ 500 ሜትር ሴቶች ውድድር ደግሞ አትሌት ሳሮን በርሔ 4 ደቂቃ ከ4 ሴኮንድ በመግባት አሸንፋለች፡፡
በተመሳሳይ በወንዶች በተደረገው የ3 ሺህ ሜትር የቤት ውስጥ ውድድር የታዋቂው የመሰናክል አትሌት ለሜቻ ግርማ ወንድም ኩማ ግርማ የግሉን ምርጥ ሰዓት በማስመዝገብ አሸንፏል፡፡
ኩማ 3 ሺህ ሜትሩን 7 ደቂቃ ከ31 ሴኮንድ ከ22 ማይክሮ ሴኮንድ በማጠናቀቅ ውድድሩን በቀዳሚነት አጠናቅቋል፡፡