አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ከኢትዮጵያ የንግዱ ዘርፍ አመራሮችና ስራ ፈጣሪዎች ጋር ውጤታማ ውይይት ማድረጋቸውን የዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይ ኤም ኤፍ) ማኔጂንግ ዳይሬክተር ክርስታሊና ጂኦርጂዬቫ ገለጹ፡፡
ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያው ለኢንቨስትመንቱ ዘርፍ መሻሻል መልካም እድል እንደሚፈጥርም ማኔጂንግ ዳይሬክተር ክርስታሊና ጂኦርጂዬቫ አመላክተዋል፡፡
የኢኮኖሚ ማሻሻያው በግሉ ዘርፍ ዕድገት ላይ እምርታ እንዲያሳይ የታክስ አሰራሩን ማዘመንና እና በዘርፉ ክትትልና ድጋፍን ማጠናከር እንደሚገባም በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት አስታውቀዋል፡፡