Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አገልግሎቱ ቀልጣፋ የትራንስፖር አገልግሎት ለመስጠት ተቋማዊ ማሻሻያ ማድረጉን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ የአውቶብስ ትራንስፖርት አገልግሎት ፈጣን እና ቀልጣፋ አገልገሎት መስጠት የሚያስችል ተቋማዊ ማሻሻያ ማድረጉን አስታወቀ።

የአዲስ አበባ ከተማ የአውቶብስ ትራንስፖርት አገልግሎት የተቋሙን አዲስ መለያ እና የስፖርት ትጥቅ አስተዋውቋል።

የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ አካሉ አሰፋ፤ ተቋሙ ከ80 ዓመታት በፊት ምስረታውን በማድረግ የትራንስፖርት አገልግሎት ሲሰጥ መቆየቱን አንስተዋል።

አሁን ላይም ከ1 ሺህ 200 በላይ አውቶብሶችን በ14 መዳረሻዎች በማሰማራት አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

አውቶብሶቹ በአዲስ አበባ ከተማ፣ ሸገር ከተማ እና በኦሮሚያ ክልል ከተሞች አካል ጉዳተኞችን፣ አቅመ ደካሞችን እንዲሁም ሌሎች የማህበረሰብ ክፍሎችን ባማከለ መልኩ አገልግሎት እየሰጡ መሆኑን ጠቅሰዋል።

አንጋፋው ተቋም ራሱን ከጊዜ ወደ ጊዜ በማሻሻል አሁን ባለበት ደረጃ መድረሱን የጠቆሙት ዋና ዳይሬክተሩ፥አሁን ላይም ፈጣን እና ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ተቋማዊ ማሻሻያ አድርጓል ብለዋል።

በቀጣይም ተቋሙ የአደረጃጀት፣ የሰው ሀይል እና የቴክኖሎጂ ማሻሻያዎችን ተግባራዊ እንደሚያደርግ አመላክተዋል።

በሚኪያስ አየለ

Exit mobile version