Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የቀድሞ የናሚቢያ ፕሬዚዳንት ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ (ኤፍ ኤም ሲ) የቀድሞ  የናሚቢያ ፕሬዚዳንት ሳም ኑጆማ በ95 አመታቸው ከዚህ አለም በሞት መለያታቸውን የወቅቱ ፕሬዚዳንት ናንጎሎ ሙቡምባ አስታውቀዋል፡፡

 

ናሚቢያ በፈረንጆቹ 1990 ነጻነቷን ካወጀች በኋላ የሀገሪቱ የመጀመሪያው ፕሬዚዳንት የነበሩት ሳም ኑጆማ ናማቢያን ከ1990- 2005 መርተዋታል፡፡

 

የቀድሞው ፕሬዚዳንት ሳም ኑጆማ ታመው በሆስፒታል ህክምና ሲደርግላቸው ቆይተው  ህይወታቸው ማለፉ ነው የተነገረው፡፡

 

የአሁኑ የናሚቢያ ፕሬዚዳንት ናንጎሎ ሙቡምባ ሳም ኑጆማ “በአያቶቻችን መሬት ላይ ባለቤት እንድንሆን ያስቻሉ እና ነጸነታችንን ያጎናጸፉን አባት ነበሩ” ሲሉ ሃዘናቸውን መግለፃቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

 

የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማህመት÷ የኬኒያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶን ጨምሮ የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች በቀድሞው ፕሬዚዳንት ህልፈት  የተሰማቸውን ሃዘን እየገለጹ ነው፡፡

 

 

 

 

 

Exit mobile version