Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ባህርዳር ከተማ ፋሲል ከነማን አሸነፈ

 

አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ዛሬ በተካሄደው የ19ኛው ዙር የኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግ መርሃ ግብር ባህርዳር ከተማ ፋሲል ከተማን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸነፈ።

ቀን 9 ሰዓት ላይ በተካሄደው በዚህ ጨዋታ ለባህርዳር ከተማ ቸርነት ጉግሳ በ46ኛው እና በ91ኛው ደቂቃ ሲያስቆጥር ለፋሲል ከተማ ደግሞ ጌታነህ ከበደ በ50ኛው ደቂቃ በፍጹም ቅጣት ምት አስቆጥሯል።

ሊጉን ኢትዮጵያ መድኅን 16 ጨዋታ ተጫውቶ በ32 ነጥብ ሲመራ ሃድያ ሆሳዕና 17 ተጫውቶ በ30 ነጥብ ሁለተኛ እንዲሁም ቅዱስ ጊዮርጊስ በተመሳሳይ ጨዋታ በ29 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃን ይዟል።

ባህርዳር ከተማ በ17 ጨዋታዎች 26 ነጥቦችን በመሰብሰብ 5ኛ ደረጃን ሲይዝ ፋሲል ከተማ በበኩሉ በ23 ነጥቦች 8ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

በሌላ በኩል ምሽት 12፡00 ወላይታ ዲቻ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር ይጫወታሉ።

Exit mobile version