አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በህገ-ወጥ መንገድ በጭነት አይሱዙ ተሽከርካሪ ሲዘዋወር የነበረ 7ሺህ 831 ሊትር ህገ-ወጥ ቤንዚን ተይዟል።
ህገ ወጥ ቤንዚኑ በአዲስ አበባ ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ከአንፎ አደባባይ ወደ ጦርሀይሎች በሚወስደው መንገድ በአይሱዙ ተሽከርካሪ ተጭኖ ሲዘዋወር በፖሊስ ሊያዝ መቻሉ ተጠቅሷል።
የተያዘውን ቤንዚን በአቅራቢያ በሚገኝ ማደያ እንዲሸጥ በማድረግ 794 ሺህ 611 ብር ከ57 ሳንቲም በፋይናንስ ዝግ አካውንት እንዲገባ መደረጉን ከአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ተመሳሳይ ድርጊቶችን ለመቆጣጠር እንዲቻል ህብረተሰቡ የተለመደ ትብብር እንዲያደርግ ጥሪ ቀርቧል።