Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ዓለም አቀፉ የመስኖና ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የልማት ጉባዔ በዚህ ሳምንት ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ የካቲት 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ዓለም አቀፉ የመስኖና ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የልማት ጉባዔ ከየካቲት 5 እስከ 7 ቀን 2017 ዓ.ም በዓድዋ ድል መታሰቢያ ይካሄዳል።

በመርሐ ግብሩ ከተለያዩ የዓለም ሀገራትና ተቋማት የተውጣጡ ከ1 ሺህ በላይ ተሳታፊዎች እንደሚታደሙ የመስኖና ቆላማ አከባቢ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

በጉባዔው በዘርፉ የሚስተዋሉ ስኬቶችና ተግዳሮቶች ላይ መሰረት ያደረጉ የምርምር ሥራዎች እንደሚቀርቡ ተመላክቷል፡፡

ኢትዮጵያ በምግብ ራስን ለመቻል፣ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከልና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ በመስኖ ስራ ያስመዘገበቻቸው ውጤቶች በተሞክሮ እንደሚቀርቡና ልምድ እንደሚቀመርባቸው ተጠቅሷል።

በአሸናፊ ሽብሩ

Exit mobile version