Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የጅቡቲ እና ሩዋንዳ የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትሮች አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 4፣ 2017(ኤፍ ኤም) የጅቡቲ እና ሩዋንዳ የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትሮች መሃመድ አሊ ዩሱፍ እና ኦሊቪየር ዣን አዲስ አበባ ገብተዋል።

ሚኒስትሮቹ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፕሮቶኮል ጉዳዮች ዳይሬክተር ጀኔራል አዚዛ ገለታ (ዶ/ር) አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በ46ኛው የአፍሪካ ሕብረት የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ስብሰባ የሚሳተፉ የተለያዩ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች አዲስ አበባ በመግባት ላይ መሆናቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው፡፡

38ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ የካቲት 8 እና 9 ቀን እንዲሁም 46ኛው የአፍሪካ ሕብረት የሥራ አስፈጻሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ የካቲት 5 እና 6 በአዲስ አበባ ይካሄዳል።

 

 

 

Exit mobile version