የሀገር ውስጥ ዜና

በመዲናዋ የሕብረቱ የመሪዎች ጉባዔ እስኪጠናቀቅ የሞተር ሳይክል እንቅስቃሴ ተከለከለ

By Feven Bishaw

February 11, 2025

 

አዲስ አበባ፣ የካቲት 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ የሚካሄደውን የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ ተከትሎ የሞተር ሳይክል እንቅስቃሴ መከልከሉን የከተማ አስተዳደሩ ትራንስፖርት ቢሮ አስታወቀ፡፡

ክልከላው ጉባዔው እስኪጠናቀቅ ማለትም ከዛሬ ጀምሮ እስከ የካቲት 9 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ እንደሚቆይ ነው የተገለጸው፡፡

በዚህ መሰረትም በተጠቀሱት ቀናት በመዲናዋ በየትኛውም አካባቢ ሞተር ሳይክል ማሽከርከር የማይቻል መሆኑን የቢሮው መረጃ ያመላክታል፡፡